አሜሪካ እና የጠፉት አስር የእስራኤል ነገዶች
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ብዙ ሀገራት የወደፊት ዕጣ የተለየ ትንቢት ይዟል። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ወይም ከግማሽ የሚበልጡት ስለ እስራኤል ሀገር እና ሕዝብ ነው።
ስለ እስራኤል የተነገሩትን እነዚህን ሁሉ ትንቢቶች ለመረዳት የእስራኤል ሕዝብ ዛሬ እነማን እንደሆኑ እና የት እንደሚገኙ ማወቅ ይኖርብናል።
ብዙ ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ ብዙ አያስቡም። ለመሆኑ በመካከለኛው ምሥራቅ “እስራኤል” የምትባል ትንሽ አገር አለች አይደል?
ብዙ ሰዎች ስለ እስራኤል የተነገሩት ትንቢቶች በሙሉ እስራኤል ስለተባለው ዘመናዊ ሕዝብ እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን ስለ እስራኤል የሚነገሩ አብዛኞቹ ትንቢቶች ከዘመናዊቷ የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ጋር በብዙ አይመሳሰሉም።
እንደ እውነቱ ከሆነ በዘመናዊው የእስራኤል ሕዝብ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የእስራኤል አካል የሆኑ አይሁዶች ብቻ ናቸው። አብዛኞቹ አይሁዶች የመጡት ከይሁዳ፣ ቢንያም እና ከሌዊ ነገዶች ብቻ ነው (1 ዜና 11፡12-14)። በጥንት ዘመን 12 የእስራኤል ነገዶች ነበሩ ። በአባቱ በያዕቆብ በረከት ምክንያት አንዱ ነገድ(ዮሴፍ)እንደ ሁለት ነገድ (ኤፍሬም እና ምናሴ) ይቆጠራል፡ ይህም በድምሩ 13 የተለያዩ ነገዶች እንዲኖሩ አድርጓል። ነገር ግን፣ ከጥቂቶች መደባለቅ በስተቀር፣ አይሁዶች የሦስቱ ነገዶች ዘሮች ስብስብ ብቻ ናቸው።
የቀሩት 10 የእስራኤል ነገዶች የት ገቡ?
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጥንታዊ የእስራኤል ሕዝብ ዝርዝር ታሪክ ይዟል። ዛሬ ሌሎቹ 10 ነገዶች የት እንዳሉ ለማወቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙትን እውነታዎች መመርመር አለብን።በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ፣ የአብርሃምን፣ የልጁን ይስሐቅን፣ እና የይስሐቅን ልጅ የያዕቆብን ታሪክ እናገኛለን።
እግዚአብሔር የያዕቆብን ስም ወደ እስራኤል ስለለወጠው (ዘፍጥረት 32፡28) ያዕቆብ “የእስራኤል ልጆች” ተብለው የሚጠሩ 12 ወንዶች ልጆች ነበሩት። እነዚህ 12 ወንዶች ልጆች ሲወልዱ፣ እነዚህ የቤተሰብ ቡድኖች 12ቱ የእስራኤል ነገዶች ሆኑ።
በመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ውስጥ እስራኤል የሚለው ስም 12ቱን ነገዶች ያመለክታል። ይሁን እንጂ እስራኤላውያን በከነዓን ምድር ከሰፈሩ በኋላ ሁለት መልከዓ ምድራዊ አቀማመጦችተከፍለዉ መጠራት ጀመሩ። የይሁዳ ነገድ በደቡብ ክልል ሰፍሮ በሰሜን ካሉት ከሌሎቹ ነገዶች የተለየ መሆን ጀመረ። አንዳንድ ጊዜ የይሁዳ ነገድ የእስራኤል አካል ተደርጎ ይወሰድ የነበረ ሲሆንበሌላ ጊዜ ደግሞ ከእስራኤል የተለየ ተደርጎ ተቀምጧል።
ንጉሥ ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ከመንገሡ ሰባት ዓመት ተኩል በፊት የይሁዳ ንጉሥ እንደ ሆነ እናስተውል (2ሳሙ 5፡5)። መጽሐፍ ቅዱስ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን “በእስራኤልና በይሁዳ ላይ ገዥ” እንደነበረ ይናገራል (1 ነገ. 1፡35)። ይሁዳ ከእስራኤል የተለየች እንደሆነች ይታሰብ እንደነበር ልብ እንበል። በዳዊት እና በሰሎሞን የግዛት ዘመን፣ እስራኤል እና ይሁዳ በአንድነት የተዋሃዱ የተለያዩ ቡድኖች ነበሩ።
መረዳት ያለብን ዋናው ነገር እስራኤልና ይሁዳ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ተለያይተው እንደነበር ነው። እነዚህ ሁለት መንግስታት አንድም ጊዜ አልተገናኙም።
አይሁዶች (አብዛኞቹ በዘመናዊው የእስራኤል ሕዝብ ውስጥ ይኖራሉ)፣ የጥንቷ የይሁዳ መንግሥት ዘሮች ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ይሁዳ የተነገሩትን ትንቢቶች ስታዩ፣ እነዚህ ትንቢቶች ስለ አይሁዶች የሚናገሩ ናቸው።
ነገር ግን ስለ እስራኤል የሚነገሩ አብዛኛዎቹ ትንቢቶች ስለ አይሁዶች ወይም ስለ ዘመናዊው የእስራኤል ሕዝብ አይደሉም። አብዛኛው ስለ እስራኤል የተነገሩት ትንቢቶች ስለሌሎች አስሩ የእስራኤል ነገዶች የተነገሩ ናቸው፣ እነዚህም ከአይሁዶች(ከዘመናዊቷ እስራኤል)ለ3000 ዓመታት ያህል ተለያይተዋል።
አስሩ የጠፉ ነገዶች
እስራኤልና ይሁዳ ሁለት የተለያዩ የሰዎች ቡድኖችን የሚያመለክቱ ከሆነ ዛሬ “የእስራኤል ህዝብ” የት ናቸዉ?
ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር ያስፈገናል።
የእስራኤል መንግሥት ንጉስ ከአይሁዳውያን ጋር ከተለየ በኋላ፣ እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ዓመታዊ በዓላት ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ቢወጡ አስሩ ነገዶች ከአይሁድ ጋር ይገናኙና እኔን ይክዱኛል ብሎ ፈራ። ስለዚህ ይህ ንጉሥ እስራኤልን ከአይሁድ ለማላቀቅ አዲስ የአምልኮ ቦታዎችንና የተለያዩ የአምልኮ ቀናትን ለአስሩ ነገድ ፈጠረ (1ኛ ነገ 12፡25-33)።
እግዚአብሔር ወደ እስራኤል እንዲመለሱ እና የሰጣቸውን ህግጋት እና የአምልኮ ቀናት እንዲጠብቁ እንዲነግሯቸዉ ብዙ ነቢያትን ወደ እስራኤል ላከ። እስራኤል ግን አልተመለሰችም። አሁንም ቢሆን የአምላክን ስም ይጠቀሙ ነበር, ነገር ግን የራሳቸውን ሰው ሠራሽ ወጎችና የአምልኮ ሥርዓቶች ይለማመዱ ነበር. ስለዚህም እግዚአብሔር በመጨረሻ በሽንፈትና በግዞት ቀጣቸው።
በ733 ዓ.ዓዘ አሦራውያን እስራኤላውያንን ድል ማድረግ ጀመሩ እና ወደ አሦር ግዛት ወደ ሰሜናዊ እና ምስራቃዊ ዳርቻ ማዛወር ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ኢዮንን፣ አቤል ቤት ማአካንን፣ ያኖአህን፣ ቃዴስን፣ አሶርን፣ ገለዓድን፣ ገሊላን፣ የንፍታሌምን ምድር ሁሉ ወሰደ። ወደ አሦርም ማርኮ ወሰዳቸው” (2ኛ ነገ 15፡29)።
ብዙም ሳይቆይ አሦራውያን የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያን ድል አድርገው የቀሩትን እስራኤላውያን አባረሩ፡- “በሆሴዕ በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ወሰደ፥ እስራኤልንም ወደ አሦር ወሰደ፥ በሐላም አኖራቸው። በሐቦር፣ በጎዛን ወንዝ፣ በሜዶንም ከተሞች ውስጥ። ከይሁዳ ነገድ ብቻ በቀር አንድም አልቀረም”(2 ነገሥት 17፡6፣ 18)።
ስለዚህ እስራኤል ከአገራቸው ተወሰዱ፣ አይሁድም ብቻ ቀሩ። አስሩ የእስራኤል ነገዶች ከተወሰዱ በኋላ ከታሪክ የጠፉ ይመስላሉ። አሁን እነሱ “የጠፉት አስሩነገዶች” በመባል ይታወቃሉ።
እስራኤል ግን ከትንቢት አልጠፋችም!
በመጽሐፍቅዱስውስጥከሚገኙትትንቢቶችውስጥከግማሽበላይየሚሆኑትስለእስራኤልየተነገሩናቸው፤ከእነዚህትንቢቶችመካከልአብዛኞቹስለ “መጨረሻውዘመን”
የተነገሩናቸው።በሕዝቅኤል37፡15-28 ያለውንትንቢትእንመልከት።ይህትንቢትእስራኤልናይሁዳበዚህዓለምፍጻሜላይእንደገናአንድህዝብእንደሚሆኑናንጉሥዳዊትምበላያቸውላይለመግዛትትንሣኤእንደሚያገኙይተነብያል።ይህትንቢትእስካሁንአልተፈጸመም።እስራኤልአሁንምከይሁዳተለይታለች። አስሩ ነገዶች አሁንምበዚህችምድርላይአንድቦታአሉ።
10 ነገዶችንእንዴትማግኘትይቻላል?
ዛሬ አስሩ ነገዶች የት እንዳሉ ማወቅ ይችላሉ? አስሩ ነገዶች ከጠፉ እንዴት ልናገኛቸዉ እንችላለን?
አሦራውያን ከእስራኤል ምድር ህዝቡን ከወሰዱ በኋላ የት እንደሄዱ ለማወቅ መሞከር እንችላለን። በታሪክ ውስጥ ጥቂት የእነርሱ አሻራዎች አሉ፡ ነገር ግን የታሪክ መዛግብት በጣም ትንሽ ናቸው እና ወደ የተሳሳተ መደምደሚያ የሚመራዎትን የግምቶች ፈለግ ሊከተሉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል! ወይም፣ እግዚአብሔር የእስራኤል ህዝብ ዛሬ የት እንዳለ እንዲያሳየን መፍቀድ እንችላለን።
የሚያስፈልገን ነገር ስለ እስራኤል ህዝብ የተነገሩት ትንቢቶች ከየትኛዉ ህዝብ ጋር ወይም ነገድ ጋር በተገናኘ እንደተፈፀመ እና እየተፈፀመ እንዳለ መመርመር ብቻ ነዉ።
ስለእስራኤልእናይሁዳቁልፍትንቢት
በዘሌዋውያን 26 ላይ የ12ቱን የእስራኤል ነገዶች የወደፊት ዕጣ የሚገልጽ ቁልፍ ትንቢት እናገኛለን። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ፣ እግዚአብሔር 12ቱ ነገዶች ለእግዚአብሔር ቢታዘዙ የሚያገኙትን በረከቶች እና እግዚአብሔርን ካልታዘዙ የሚመጡባቸዉን የእርግማን ቅደም ተከተሎች ይዘረዝራል።
በዘሌዋውያን 26 ላይ የተነገሩት ብዙዎቹ በረከቶች ለእስራኤል ህዝብ የመጡት በንጉሥ ዳዊትና በንጉሥ ሰሎሞን የግዛት ዘመን ነው። በዚያን ጊዜ የአሦርና የግብፅ ንጉሠ ነገሥታት በድክመት ውስጥ ነበሩ፣ እና ለተወሰኑ አሥርተ ዓመታት እስራኤል በዓለም ላይ እጅግ ባለጸጋ እና ከፍተኛ ተደማጭነት ያላት ሕዝብ ነበረች።
ነገር ግን በሰሎሞን የግዛት ዘመን ማብቂያ አካባቢ፣ ንጉሡ ከእግዚአብሔር ርቆ ለሌሎች አማልክቶች ቤተ መቅደሶችን ሠራ (1 ነገ 11፡4-10)። ሰዎቹም የእሱን ምሳሌ በመከተል ከእግዚአብሔር መራቅ ጀመሩ።
እግዚአብሔር በዘሌዋውያን 26 ላይ ቃል እንደገባው፣ 12ቱን ነገዶች ብሄራዊ በረከታቸውን በማንሳት ቀጥቷቸዋል። በሰሎሞን የግዛት ዘመን የመጨረሻዎቹ ዓመታት ጠላቶች በዙሪያቸው መነሳት ጀመሩ (1 ነገ 11፡14-25)።
ሰሎሞን የሞተዉ በ931 ዓ.ዓ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ እስራኤል እና ይሁዳ ለሁለት ተከፍለው፣ ሁለት ደካማ አገሮች ሆኑ (1 ነገ. 12)። በጥቂት ዓመታት ውስጥ፣ ግብፃውያን ይሁዳን ወረሩ እና ብዙ ሀብታቸውን ወሰዱ (1 ነገ 14፡25-26)።
ቀደም ሲል እንዳየነው፣ አሦራውያን እስራኤላውያንን ድል ማድረግና ማባረር የጀመሩት ከ200 ዓመታት በኋላ ማለትም በ733 ዓ.ዓ አስሩ ነገዶች ወደ መሬታቸው አልተመለሱም። አይሁዶች ብቻ ቀሩ!
ከዚያም በ605 ዓ.ዓ ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ያዙ እና አይሁዶችን ወደ ባቢሎን ማጋዝ ጀመሩ። አንዳንድ አይሁዶች ከ70 ዓመታት በኋላ ወደ አገራቸው ተመለሱ፣ አብዛኞቹ ግን አልመለሱም። አብዛኞቹ አይሁዶች በመጨረሻ ወደ ሰሜን ወደ አውሮፓ ተሰደዱ፣ እዚያም እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ቆዩ።
በ1916 የአይሁዶች ሁኔታ በድንገት መለወጥ ጀመረ። ዓለም በአንደኛው የዓለም ጦርነት መሃል ላይ በነበረበት ወቅት እንግሊዝ እና ፈረንሳይ የሳይክስ-ፒኮት ስምምነት የሚል ሚስጥራዊ ስምምነት አደረጉ። ይህ ስምምነት የኦቶማን መንግስትንን ቢያሸንፉ መካከለኛውን ምስራቅ እንዴት እንደሚከፋፈሉ ይገልጻል። በዚህ ስምምነት የእስራኤልን አሁናዉ ምድር አካባቢ እንደ ልዩ ዓለም አቀፍ ክልል አስቀምጠዋል። ከዚያም በሰኔ ወር 1916 እንግሊዞች አረቦች በኦቶማን ገዥዎቻቸው ላይ እንዲያምፁ ረዱዋቸው።
በታህሳስ 1917 የእንግሊዝ መንግስት የባልፎር የተባለዉን መግለጫን አሳተመ፡ በዚህም አይሁዶች “ወደ አሁኑ መኖሪያ ምድራቸዉ እንዲሰበሰቡ” እንደሚደግፉ አስታወቁ፡፡ ከዚያ በኋላ እንግሊዞች ወዲያውኑ ምድሪቱን ወርረው እየሩሳሌምን ያዙ። እነዚህ ክንውኖች በመጨረሻ በ1948 ዘመናዊዉ የእስራኤል ሕዝብ እንዲመሠረት ምክንያት ሆነዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዶች ወደ እስራኤል ምድር ተመልሰዋል።
እስራኤልተመልሳለች?
የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት የሚያጠኑ ብዙ ሰዎች የእስራኤል ሕዝብ መቋቋሙንና አይሁዳውያን ወደ ጥንት አገራቸው መመለሳቸው በመጨረሻው ዘመን ስለ እስራኤል መሰብሰብ የተነገሩት ጥንታዊ ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን እንዳገኙ ያምናሉ። ሆኖም እነዚህ ትንቢቶች ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ናቸው። እነዚያ ትንቢቶች ገና አልተፈጸሙም! አስሩ ነገዶችና አይሁዶች በዘመኑ ፍጻሜ ተሰብስበው ወደ አንድ ሕዝብ ይቀላቀላሉ፣ በንጉሥ ዳዊት በትረ መንግስት ይገዛሉ።
ነገር ግን፣ የብዙ አይሁዶች ወደ ምድሪቱ መመለሳቸው እና የዘመናዊቷ የእስራኤል ሀገር መመስረት በዘሌዋውያን 26 ላይ ያለውን ትንቢት ፈጽሟል።
በዘሌዋውያን 26 ላይ፣ እግዚአብሔር 12ቱ ነገዶች ከእርሱ ቢርቁ በመጀመሪያ ሽብር፣ ደዌ እና በጦርነት እንደሚሸነፉ ተናግሯል (ዘሌ 26፡16-17)። በኋላ፣ ብዙ ቅጣቶች ይመጣሉ፣ በመጨረሻም ነገዶቹ ከምድራቸው ይወሰዳሉ (ዘሌዋውያን 26፡32-39)።
እግዚአብሔር በሚስጥር መንገድ፣ ይህ ቅጣት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ተንብዮአል፡- “ይህ ቢሆንም ባትሰሙኝ፣ ነገር ግን በእኔ ላይ ብትሄዱ፣ እኔ ደግሞ ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት ጊዜ እቀጣችኋለሁ” (ዘሌዋውያን 26፡- 27-28)።
አምላክ 12ቱን ነገዶች “ለሰባት ጊዜ” እንደሚቀጣ ተናግሯል። በክፍል 1 “ሰባት ጊዜ” ማለት 2520 ቀናት ወይም 2520 ዓመታት ማለት እንደሆነ ተምረናል። ያ ግልጽ ካልሆነ፣ ራእይ 11:2-3 (42 ወራት እና 1260 ቀናት) ከራእይ 12:14 (3 ½ ጊዜ) እና ራእይ 13:5 (42 ወራት) ጋር ያወዳድሩ። ከዚያም ዘኍልቍ 14:34 እና ሕዝቅኤል 4:6ን ያንብቡ፤ እነዚህም ሁለቱም በትንቢት ውስጥ አንድ ቀን ብዙውን ጊዜ አንድ ዓመት እንደሚያመለክት ያሳያሉ።
ዘሌዋውያን 26 አምላክ አይሁዳውያንንና ሌሎቹን 10 ነገዶች ለኃጢአታቸው “ሰባት ጊዜ” እንደሚቀጣ ተንብዮአል። ይህም ማለት ቅጣቱ ለ 2520 ዓመታት ይቆያል፡፡
አይሁዶች ከምድራቸው መወሰድ የጀመሩት በ605 ዓ.ዓ ነዉ፡ 2520 ዓመታትን ወደ 605 ዓ.ዓ ከደመሩ ስሌቱ ወደ 1916 ዓ.ም ያደርሳል - አይሁዶች ወደ አገራቸው የሚመለሱበት ትክክለኛው ጊዜ እንደገና መከፈት የጀመረበት ጊዜ ነው!
ሰባት ጊዜ የተነገረው ትንቢት በተያዘለት ጊዜ ተፈጽሟል። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ትክክል መሆናቸውን ከሚያሳዩ በርካታ ማስረጃዎች አንዱ ነው።
ዛሬ 10 ቱነገዶችየትናቸዉ?
አሁን የዘመኑን የእስራኤል ህዝብ ለማግኘት የሚያስፈልግ ቁልፍ አለን፡ ሰባቱ የቅጣት ጊዜያት ለእስራኤል መቼ እንዳበቃ አስልተን እና በዚያን ጊዜ የትኞቹ ህዝቦች መነሣት እንደጀመሩ ለማወቅ ታሪክን መመልከት።
እግዚአብሔር የእስራኤልን ህዝባዊ በረከቶች “ሰሎሞን በሸመገለ ጊዜ” (1 ነገሥት 11፡4) በወሰደ ጊዜ የእስራኤል ቅጣት እንደጀመረ አይተናል። ሰሎሞን በ931 ዓ.ዓ በ70 ዓመቱ ሞተ። በሰሎሞን ሕይወቱ መጨረሻ ላይ ንስሐ ገብቶ የመክብብ መጽሐፍ ጻፈ። ስለዚህ ምክንያታዊ ግምት ይህ የቅጣት ጊዜ የጀመረው ሰሎሞን ከመሞቱ ከአምስት ዓመታት በፊት ማለትም በ936 ዓ.ዓ አካባቢ ነው። (በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ይህን ቀን የሚደግፍ ትንቢትም አለ።)
2520 ዓመታትን ወደ 936 ዓ.ዓ ከጨመሩ ወደ በ1585 ዓ.ም ያደርሳል።
በ 1585 ጉልህ የሆነ ነገር ተከስቷል**? አዎ!
እ.አ.አ. በ1580 የስፔኑ ንጉስ ፊሊፕ 2ኛ የስፔን እና የፖርቱጋል ግዛቶችን በግዛቱ ስር አንድ አደረገ። ይህ ጥምር መንግስት በአለም ዙሪያ ተዘረጋ። ፊሊፕ በመላው አውሮፓ ብዙ ህዝቦችን ይገዛ የነበረው የኃያሉ የሃፕስበርግ ቤተሰብ አባል ነበር። ብዙም ሳይቆይ ሃፕስበርግ መላውን አውሮፓ ሊቆጣጠር እንደሚችል ታየ።
በ 1585 ንጉስ ፊሊፕ II ኔዘርላንድስን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እና በፈረንሳይ እና በእንግሊዝ ላይ ያለውን ቁጥጥር ለማራዘም ዘመቻ ጀመረ፡ ነገር ግን የፊሊፕ እቅዶች ወደ ኋላ ቀሩ፣ እና 1585 የሃፕስበርግ የአውሮፓ እና የአለም የበላይነት የመጨረሻው መጀመሪያ ነበር።
በ1584 የመጨረሻ ቀን ፊሊፕ በፈረንሳይ ከሚገኘው የካቶሊክ ሊግ ጋር ሚስጥራዊ ስምምነት አደረገ። ይህ ስምምነት በፈረንሳይ ውስጥ የሚፈቀደው ብቸኛው ሃይማኖት ካቶሊካዊነት መሆኑን ገልጿል። በከፊል የፕሮቴስታንት ሄንሪ ናቫሬ ንጉስ እንዳይሆን ለመከላከል የተደረገ ሙከራ ነበር። እንግሊዛውያን ውሉን ሲያውቁ ፕሮቴስታንትነትን በመላው አውሮፓ ለማጥፋት የተደረገ ሙከራ አካል ነው ብለው ፈሩ።
ከዚያም በነሐሴ 1585 ፊሊፕ በኔዘርላንድ ከሚገኙት የፕሮቴስታንት ዓመፀኞች አንትወርፕን መውሰድ ቻለ። ነገር ግን የእሱ ድል በመጨረሻ ወደ ስፔን ውድቀት አመራ። ስፔናውያን አንትወርፕን ከያዙ ከጥቂት ቀናት በኋላ ፕሮቴስታንት እንግሊዛዉያን የደች አማፂያንን ለመደገፍ ስምምነት ፈፀሙ። ይህ በእንግሊዝና በስፔን መካከል ጦርነት አስነሳ። ከአንትወርፕ ውድቀት በኋላ፣ ደች እንደገና ተሰብስበው በፍጥነት ተነስተው በዓለም ላይ ግንባር ቀደም የፋይናንስ ኃይል መሆን ችለዋል።
ፊሊፕ በፈረንሳይ ፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ያደረገው ሙከራም ከሽፏል። ሄንሪ ናርቫሬ የፈረንሳይ ንጉስ ሆነ፣ በፈረንሳይ ውስጥ ላሉት ፕሮቴስታንቶች እውቅና እና ሃይማኖታዊ መቻቻልን ሰጠ እንዲሁም ከእንግሊዝ እና ከደች ጋር በስፔን ላይ ተሰልፏል። ይህ ፈረንሳይ በዓለም ላይ ግንባር ቀደም ሃይል ሆና ስፔንን ለመተካት የጀመረችበት ጅምር ነበር።
ስፔን ከእንግሊዝ ጋር ያደረገችው ጦርነትም አልተሳካም። እ.ኤ.አ. በ1588 እንግሊዛውያን እንግሊዝን ለመቆጣጠር እና በካቶሊክ ቁጥጥር ስር እንድትሆን ለማድረግ ስፓኒሽ ያደረጉትን ሙከራ ከለከለ። ከ 1585 ጀምሮ እንግሊዝ ወደ ታላቅ የባህር ኃይል እና ቅኝ ግዛት ማደግ ጀመረች፡፡ ውሎ አድሮ የእንግሊዝ ኮመንዌልዝ ፈረንሳይን በዓለም ላይ ግንባር ቀደም ሃይል አድርጎ ተካት። ከእንግሊዝ አሜሪካን ቅኝ ግዛቶች ማድረግ በኋላ አሜሪካ በዓለም ላይ ግንባር ቀደም ኃያል ሀገር ለመሆን በቃች።
እ.አ.አ. በ1585 በዓለም አቀፍ ደረጃ አስደናቂ ለውጥ እንደጀመረ ልብ ይበሉ። የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ አገሮች በድንገት ሁሉም ዕድል ያላቸው ይመስሉ ነበር። በዚህ ጊዜ ውስጥ የዴንማርክ እና የኖርዌይ መንግሥት (አይስላንድን ጨምሮ) ታዋቂ ኃይል ሆነ። የስዊድን መንግስት ከአውሮፓ ታላላቅ ኃያላን መንግስታት አንዱ ሆነ። በተከታዮቹ 400 ዓመታት ውስጥ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ አገሮች እና ቅኝ ገዥዎቻቸው በዓለም ላይ ካሉት ሀብቶች ከግማሽ በላይ የሚቆጣጠሩት የዓለም እጅግ ሀብታም አገሮች ሁኑ። እ.ኤ.አ.
በ1585 እና ከዚያ በኋላ የተከናወኑት ድርጊቶች ለእስራኤል የሰባቱን የቅጣት ጊዜያት የመጀመሪያ ምዕራፍ አብቅተዋል።
አያስገርምም?
እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ ብሎታል፡- “አንተ የብዙ አሕዛብ አባት ትሆናለህ…አሕዛብንም አደርግሃለሁ ነገሥታትም ከአንተ ዘንድ ይመጣሉ።” (ዘፍጥረት 17:4, 6) እግዚአብሔር 12ቱን ነገዶች “ከምድር አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ እንደሚያደርጋቸው ተናግሯል” (ዘዳ 28፡1)። እነዚህ ተስፋዎች ተፈጽመዋል።
ያስተዉሉ። በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ አገሮች እና በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውስትራሊያ፣ በኒውዚላንድ እና በደቡብ አፍሪካ ያቋቋሟቸውን ቅኝ ግዛቶች የተትረፈረፈ ሀብት ያጋጠማቸው ሌሎች ብሔሮች በታሪክ ውስጥ ይኖር ይሆን?
እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተናገረው ትክክለኛ ጊዜ ላይ የትንቢቱን ፍፃሜ ያገኘ ሌላ የህዝብ ስብስብ ይኖር ይሆን?
የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ አገራት ያመጡት ፈጣን እድገት እና ለ 400 ዓመታት ያካበቱት ሥልጣን ፣ ሀብት እና ተጽዕኖ የማይካድ የታሪክ እውነታዎች ናቸው።
ዛሬ የጠፉት አስሩ ነገዶች የት አሉ? ስለ እስራኤል የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻ ዘመን ትንቢቶች የትኞቹ ህዝቦች ናቸው? እውነታውን ይመርምሩ እና ለራስዎ ይወስኑ።
የበለጠ ማስረጃ
ያስታውሱ የአስርቱ ነገዶች ሁለተኛ የቅጣት ምዕራፍ የተጀመረው አሦራውያን እስራኤልን ከምድራቸው ማባረር በጀመሩበት በ733 ዓ.ዓ ሲሆን ይህ የቅጣት ምዕራፍ በትክክል ከ2520 ዓመታት በኋላ በ1788
አብቅቷል። እና በ 1788 ምን ሆነ? እ.ኤ.አ. በ 1788 የእንግሊዘኛ ተናጋሪ አገራት ህዝቦች በድንገት መነሳትን ያሳያል፡፡
እነዚህን እውነታዎች ይመልከቱ፡-
- አውስትራሊያ መቼ ነው የተመሰረተችው? በጥር 26 ቀን 1788 እ.ኤ.አ.
- ካናዳ የተቋቋመው መቼ ነው? በ1791፣ በ 1788 በኩቤክ የመጀመሪያዎቹ የእንግሊዝ የአስተዳደር አውራጃዎች ከተቋቋሙ ከሶስት ዓመታት በኋላ።
- እንግሊዝ በዓለም ላይ መሪ የሆነችው መቼ ነው? በ 1788 ፈረንሳይ ወደ ፈረንሳይ አብዮት መንሸራተት ስትጀምር
- አሜሪካ መቼ ተወለደች? የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሰኔ 21 ቀን 1788 ሲፀድቅ።
ይህ በጊዜው የተፈጸመ ሌላ አስደናቂ ትንቢት ነው።