በመጨረሻ ዘመን ክስተቶች ውስጥ የጀርመን ሚና

እ.ኤ.አ በ2022 የሩሲያ ዩክሬን ወረራ ዓለምን አስደንግጧል፡፡ የፑቲን የኒውክለር ጥቃት ዛቻ የሶስተኛውን የዓለም ጦርነት ፍራቻን አነሳስቶአል፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ የጀርመኑ ቻንስለር የጀርመን ጦር ለመገንባት 100 ቢሊዮን ዩሮ እንደሚያወጣ ቃል ገባ በአውሮፓ ዳርቻ ላይ ያሉ መንግሥታት የአውሮፓ ህብረት የኔቶ አባል ለመሆን ፍለጋ ጀምረዋል፡፡

እነዚህ ክስተቶች ወዴት ያመራሉ? የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ስለ አውሮፓ ስለ ሩሲያ እና ስለሌላው ዓለም የወደፊት ዕጣ ምን ይላል?

የመጨረሻ ዘመን ባቢሎን

የራዕይ መጽሐፍ ስለ ታላቋ ከተማ ‹‹ባቢሎን›› ‹‹በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ›› ናት በማለት ስለ መጨረሻው ዘመን ይናገራል፡፡ (ራዕይ 17፡5፣ 18) ይህቺ ባቢሎን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት በፊት ዓለምን የሚገዛ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሃይማኖት ኃይልን ትወክላለች፡፡ (ራዕይ 18)

ይህች የዘመናችን ‹‹ባቢሎን›› የምትገኘው የት ነው? ይህ ዓለምን የሚገዛው የፖለቲካና የሃይማኖት ኃይል በዓለም መድረክ ላይ የሚታየው መቼ ነው? መልሱ በዳንኤል ምዕራፍ 4 ውስጥ ይገኛል፡፡

ይህ ጥንታዊ ትንቢት ባቢሎን አሁን እንዳለች ያሳያል፡፡ ‹‹ንጉሱም ከሰማይ የወረደውንና ዛፉን ቁረጡ አጥፉትም ነገር ግን ጉቶውን በምድር ውስጥ ተውት በብረትና በናስ ማሰሪያ ታስሮ በመስክ ውስጥ ይቆይ በሰማይም ጠል ይረስርስ ሰባት ዘመናትም እስኪያልፉበት ድረስ እድል ፈንታው ከምድር አራዊት ጋር ይሁን ያለውን ቅዱስ ጠባቂ ማየቱ ንጉሥ ሆይ ፍቺው ይህ ነው፡፡ በጌታዬ በንጉስ ላይ የወረደው የልዑል ትዕዛዝ ነው፡፡ ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን ለሚወደደውም እንዲሰጠው እስኪታወቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ መኖርያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፡፡ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ በሰማይም ጠል ትራሰርሳለህ ሰባት ዘመናትም ያልፍብሀል የዛፉንም ጉቶ ይተውት ዘንድ ማዘዙ ሥልጣን ከሰማያት እንደሆነ ካወቅህ በኋላ መንግሥትህ ይቆይልሀል፡፡›› (ዳንኤል 4፡23-26)

አንድ ዓመት በኋላ ይህ ትንቢት ተፈፀመ እግዚአብሔር ቡከደነፆት ለትዕቢቱ ቅጣት ይሆን ዘንድ አዕምሮውን እንዲያጣ አደረገው ከዚያም በሰባት ዓመቱ መጨረሻ ንጉሱ ወደ አእምሮው ተመልሶ የባቢሎንን ግዛት ለመግዛት ተመለሰ፡፡

ይህ ትንቢት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተፃፈው ለምንድን ነው?

ዳንኤል ይህ ትንቢት ፍጻመውን ካገኘ በኋላ እንዳልፃፈው አስታውሱ፣ ስለዚህ ይህ ትንቢት ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምንም አይነግንም ለኋለኛው ዘመን ሁለተኛ ፍፃሜውን ካልተናገረ በቀር በእርግጥም ሁለተኛ ፍፃሜ ሆነ ባበሎን ለሰባት ‹‹ጊዜያት›› ገዥ እንዳጣት አእምሮውን ሲያጣ ባቢሎንም ለሰባት ‹‹ጊዜያት›› ገዥ ያጣችበት ሁለተኛ ጊዜ ነበር እና ‹‹ጊዜ›› ምንድን ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ውስጥ ጊዜ 360 ቀናትን ያመለክታል እንዴት እናውቃለን?

ራዕይ ምዕራፍ 11፡2-3 ‹‹42-ወራት›› እና ‹‹1260 ቀናት›› ተብሎ የተገለጸውን ጊዜ ይጠቅሳል፡፡ በራዕይ ምዕራፍ 12፡14 ያው የጊዜው ዘመን ‹‹ጊዜና ዘመናት ግማሽ ጊዜ›› (1 + 2 + ½ 3½ ጊዜ) ይባላል፡፡ ሒሳብ ከሠራን አንድ ጊዜ 360 ቀናት ሆኖ እናገኛለን፡፡

የዳንኤል 4ን ሁለተኛ ፍፃሜ ለመረዳት በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ውስጥ ‹‹1ቀን›› ብዙውን ጊዜ አንድ ዓመት እንደሚያመለክት ማወቅ አለብን፡፡ ይህንን ራሳችን ለማረጋገጥ ዘኅልቁ 14፡34 እና ሕዝቅኤል 4፡ 6ን አንብቡ፡፡

በዳንኤል ምዕራፍ 4፡4 የመጀመሪያ ፍፃሜ ባቢሎን ለ2520 ቀናት መሪ አልባ ሆና ነበር (7 x 360 = 2520) ማለትም ሰባት ዓመት ገደማ ነው፡፡ በሁለተኛው ፍፃሜ ላይ ባቢሎን ለ2520 ዓመታት መሪ ሆና ነበር፡፡ አምላክ የጥንቱን የባቢሎናውያን ግዛት ቆርጦ ግንዱ ለ2520 ዓመታት እንዳያድግ የብረት ማሰሪያ አደረገ፡፡ ነገር ግን በዚያ ‹‹ሰባት ዘመናት›› መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር የብረት ማሰሪያውን አስወገደ፡፡ በዚያን ጊዜ አዲስ መሪ ወደ ስልጣን ወጣ፣ በራዕይ መጽሐፍ ላይ የተገለፀው ‹‹ባቢሎንም›› እንደገና ማደግ ጀመረች፡፡ ‹‹ባቢሎን›› አሁንም እያደገች ነው፡፡ በዓይን ፊት እና መላውን ዓለም እስክትቆጣጠር ድረስ ማደጉን ትቀጥላለች፡፡

ይህ መቼ ሆነ?

በዳንኤል ምዕራፍ 4 ላይ ከናቡከነፆር ህልም በኋላ ያለውን እናስተውል፣ የሚቀጥለው ምዕራፍ የጥንቱን የባቢሎን ግዛት ውድቀትን ለመግለፅ በጊዜ ወደፊት ይዘልላል (እንደ አብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የዳንኤል መጽሐፍ በጥብቅ የጊዜ ቅደም ተከተል ሳይሆን በጭብጥ የተደራጀ ነው)፡፡

የባቢሎን አለቆች ግብዣ እያደረጉ ሳለ አንድ እጅ መጥቶ በቅጥሩ ላይ መልዕክት ፃፈ፣ ንጉሡም መልዕክቱን እንዲያነብና እንዲያስረዳ ዳንኤልን ጠራው ዳንኤል በግድግዳው ላይ የተፃፈው ጽሑፍ የባቢሎን መንግሥት እንዳበቃና አምላክ ለሜዶንና ለፋርሳውያን እንደሰጣቸው የሚያመለክት እንደሆነ ገለፀ፡፡ በእርግጥም ሜደናውያንና ፋርሳውያን መንግሥቱን አሸንፈው ነበር፣ በዚያም ሌሊት የባቢሎንን ከተማ ወረሩ በናቦኒዶስ ዜና መዋዕለ ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን ትክክለኛ ቀን እናገኛለን፡፡ ናቦኒዶስ እንደሚለው ‹‹በአሥራ አራተኛው ቀን ሲፓር በጦርነት ተማረከ›› ናቦኒደስም ኡግባሩና የቂሮስ ሠራዊት ያለጦርነት ወደ ባቢሎን ገቡ፡፡ ሲፖር የተማረከው በባቢሎን ወር ቲሸርቱም በ14ኛው ቀን በ539 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነበር፡፡

ከሁለት ቀን በኋላ ዳንኤል ለባቢሎን ገዥዎች ባቢሎን ለሜዳንና ለፋሳውያን ተሰጥታ እንደነበረች እና ከዚያም ሌሊት የባቢሎን ከተማ እንደወደቀች ነገራቸው፡፡ ስለዚህ እዚህ ከጥንታዊው የሸክላ ሠሌዳ ላይ የመጀመሪያውን ትክክለኛ ቀን አግኝተናል፡፡ ባቢሎን ያለ ገዥ የምትሆነው በ2520 ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ ይህ ጊዜ የሚያበቃበትን ትክክለና ቀን ከማሰላታችን በፊት በግድግዳው ላይ በተፃፈው ጽሑፍ ላይ የዚህን የ2520 ዓመታት ጊዜ ሌላ ፍጥጫ ማግነታችንን ልብ በሉ፡፡ ጽሕፈቱም፡፡

‹‹ማኔ ቴቄል እና ፋሬስ›› የሚል ነበር፡፡ (ዳንኤል 5፡25) የግርግር ማስታወሻዎች ያሉት መጽሐፍ ቅዱስ ካለ እነዚህ ቃላት እንደ ገንዘብ ክፍል ሲገልጹ ልታዩአቸው ትችላላችሁ፡፡

‹‹ማኔ›› ሚና ሲሆን ይህም 50 ስቅል ነው፡፡ ‹‹ቴቄል›› ስቅል ነው፡፡ ‹‹ፋሬስ›› ማለት ‹‹ተከፋፍሏል›› ወይም ‹‹ግማሾች›› እና ግማሽ ምንን ያመለክታል እሱም 25 ስቅል ነው፡፡ ይህንን ስትጨምሩበት 50 + 50 + 1 + 25 126 ስቅል ነው፡፡ ዘፀአት 30 13 ‹‹አንድ ስቅል›› 20 አቦሊ ነው፡፡ 126 ስቅል በ20 ማባዛት እና 2520 አበሊ ያገኛሉ፡፡ ያም በዳንኤል 4 ላይ ስላው ‹‹ሰባት ዘመን›› ከተነገረው ትንቢት ያገኘነው ትክክለኛ ቁጥር ነው፡፡ አሁን በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ውስጥ ያሉት ቀኖች ሁልጊዜ የዕብራይስጥ የጊዜ መቁጠሪያ እንደሚጠቀሙ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

በባቢሎን አቀጣጠር ቲሽርቱም የሚለው ወር በዕብራይስጥ አቆጣጠር ከቲሽሪ ወር ጋር እኩል ነው፡፡ ስለዚህ የሲፑር ከተማ በቲሽሪ 14፣ 539 ከክርስቶስ ልደት በፊት ወደቀች ከሁለት ቀን በኋላ ዳንኤል የባቢሎን መንግሥት ለሜዶንና ለፋርስ ተሰጥቷል አለ፡፡ ስለዚህ ቁጥራችንን በቲሽሪ 14,539 ከክርስቶስ ልደት በፊት እንጀምራለን፡፡ 2520 ዓመታት ስትጨምሩ ወደ ቲሽሪ 14,1982 ዓ.ምህረት ያመጣናል፡፡

እናንተ እንዲህ ልትጠይቁ ትችላላችሁ?

539 ዓመተ ዓለም+1982 ዓመተ ምህረት ሲደመሩ 2521 አይደለም? አዎ ነገር ግን ከ1 ዓመተ ዓመት በፊት እና 1 ዓመተ ምህረት መካከል ዜሮ ዓመት አልነበረም፡፡ ስለዚህ ከአንድ ዓመተ ዓለምና ከአንድ ዓመተ ምህረት መካከል ያለው ጊዜ አንድ አመት ነበር፡፡ እንጂ በ1 ዓመተ ዓለም ላይ አንድ ዓመተ ምህረት ሲደመር ሁለት ዓመት አልነበረም፡፡

የዕብራይስጥን ካላንደር ብንመረምር ቲሽሪ 14,1982 ጥቅምት 1 ላይ እንደወደቀ እናገኛለን፡፡ አሁን በጥቅምት 1,1982 የሆነውን ነገር ለማወቅ በዜና ላይ ፈልጉ፡፡ ምን አገኛችሁ? ስለ ጀርመን ቻንስለር የሆነ ነገር? ትክክል ነው፡፡ የምዕራብ ጀርመኑ ቻንስለር በድንገት በሄልሙት ኮል ተተኩ በምርጫ ሳይሆን ገንቢ በሆነ ያለመተማመን ድምፅ ነበር፡፡ በጀርመን ታሪክ በዚህ ያልተለመደ ዘዴ መሪ ወደ ሥልጣን የመጣበት ይህ ብቸኛው ጊዜ ነበር፡፡

ጀርመን አለምን ትመራ ይሆን?

በጥቅምት 1, 1982 የሄልሙት ኮል ድንገተኛ ያልተጠበቀ በስልጣን ላይ መውጣት በዳንኤል 4 ላይ ያለው ትንቢት ሁለተኛ ፍፃሜ ነበር?

የሚከተሉትን እውነታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ለራሳችን እንወስን፡፡

  • ልክ ከስምንት አመታት በኋላ በኩል አመራር ምስራቅ እና ምዕራብ ጀርመን የተቀላቀሉት ኮል ስልጣን በያዘበት ቀን ነው፡፡ ቲሽሪ 14 እርስዎ ጥቅምት 3,1990 ነበር፡፡
  • ኮል የምስራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ውህደት ዋና ተሟጋች ነበር፡፡ እርሱ የማስተርችት ስምምነት ከሁለቱ ዋና አርክቴክቶቸ አንዱ ነበር፡፡ ይህ ስምምነት የአውሮፓ ህብረትን በመመስረትና የአውሮፓ ህብረትን ለመቀላቀል ዩሮን የአውሮፖ የጋራ ምንዛሬ አድርጎ አቋቋመ፡፡
  • ኮል እና ተተኪዎቹ ጀርመንን በአውሮፓ ቀዳሚ ሃይል አድርገው አቋቁመው አውሮፓን በዓለም ላይ ቀዳሚ ኃይሉ ለማድረግ እየሰሩ ነው፡፡ (አላፍ፣ ቮልትዝ ይመልከቱ ጀርመን ዓለምን መምራት አለብን) እነዚህ ተከታታይ ክስተቶች ከ2500 ዓመታት በፊት በተነገረለት ትክክለኛ ቀን የመጀመር እድላቸው ምን ያህል ነው?

በዳንኤል 4 ላይ ያለው ትንቢት የተቆጠረውን በዛፉ ግንድ ላይ ስለተሠራ የብረት መሣሪያ እንደሚገልጽ አስታወሱ የብረት መሳሪያው በጥቅምት 2,1982 ከተወገደ በኋላ አዲስ የዓለም ኃይል መንግሥት የሆነችው አዲሲቷ ‹‹ባቢሎን›› ከጥንቷ ባቢሎን ሥሮች መውጣት ጀመረች፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት ትንቢቶች በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት የተፃፉ ናቸው እነ እግዚአብሔር አንድ ነገር አንደሚሆን ሲናገር በጊዜው በትክክል እንዲፈፀም ያደርጋል፡፡

21ኛው ክፍለ ዘመንን ማን ይገዛዋል?

በጀርመን የምትመራ አውሮፓ ከኃይል የሃይማኖት ድርጅት ጋር በመሆን ስለ ባቢሎን መጨረሻ የሚነገሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ፍፃሜያቸውን ያገኛሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት እንደሚያሳየው ይህች ‹‹ብቢሎን›› በመጨረሻ ሩሲያን፣ ቻይናንና የተቀረውን ዓም ያካተተውን ዓለም አቀፉው ግዛት ትቆጣጠራለች፡፡ በወደፊት ትምህርቶች ስለዚህ ግዛት እና በመጨረስ ዘመን ክስተቶች ውስጥ ግንባር ቀደም ሚና ስለሚጫወቱ 10 የዓለም መሪዎች የበለጠ ትማራላችሁ፡፡

ለአሁን እያደገች ያለችው ባቢሎን ጀርመንና አውሮፓን አንድ የሚያደርጋቸው ሃይማኖታዊ ድርጅት ለሩሲያ ስጋት እንዴት ምላሽ እንደሰጠ እንመልከት ቀጣዩ ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች ግማሹን የሚከፍተውን ቁልፍ ይሰጣል፡፡ አሁን የተማራችሁትን በትክክል እንደሚናገር በራስ ለማረጋገጥ ሁሉንም ዳንኤልን መጽሀፍ ምዕራፍ 4 ማንበብን አትዘንጉ፡፡

እባክዎትን ይህንን የትንቢት ዜና መጣጥፍ በማህበራዊ ገፅ ላይ ለጓደኞችዎ ያካፍሉ፡፡